Startseite Podcasts ማሕደረ ዜና
ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና

DW 100 Folgen Sep 14, 2026

ማሕደረ ዜና በየሳምንቱ ሰኞ የሚቀርብ የዜና ትንታኔ ፖድካስት ነው። በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የተከሰቱ፣ የሚከሰቱ እና የተነገሩ ዋና ዋና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ዝግጅቱ የሀገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማህበራትን፣ ድርጅቶችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት ተግባራትን በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ያቀርባል። አዘጋጁ ነጋሽ መሐመድ ነው።

Folgen

ማሕደረ ዜና፣ የመስከረም 11፣ 2001 ጥቃት ዝክር-«ጦርነቱ ይቀጥላል» ትራምፕ
ማሕደረ ዜና፣ የመስከረም 11፣ 2001 ጥቃት ዝክር-«ጦርነቱ ይቀጥላል» ትራምፕ Sep 14, 2026 14:27 ጥቃቱ ሲፈፀም ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ ሳራሶታ፣ ፍሎሪዳ የአንድ ትምሕርት ቤት ተማሪዎችን እያነጋገሩ ነበር።ፕሬዝደንቱ ከመሩት የመልዕክተኞች ጓድ ጋር አብሮ የተጓዘዉ ጋዜጠኛ ስቲቭ ሆላንድ እንደሚያስታዉሰዉ ቡሽ ከኒዮርኩ ሕንፃዎች የመጀመሪያዉ መመታቱን ሲሰሙ «የፓይለት ስሕተት ነዉ» ብለዉ ነበር።ሁለተኛዉ መደገሙ ሲነገራቸዉ ግን ፊታቸዉ ተለዋወጠ።
የጀርመንዋ ዛክሲሶንያ ግዛት ምርጫ ዉጤት በአዉሮጳ ፖለቲካ ላይ ያለዉ አንድምታ
የጀርመንዋ ዛክሲሶንያ ግዛት ምርጫ ዉጤት በአዉሮጳ ፖለቲካ ላይ ያለዉ አንድምታ Sep 7, 2026 12:38
ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የእስራኤል መሪዎች የጫሩት ጦርነት 6ኛ ወር
ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የእስራኤል መሪዎች የጫሩት ጦርነት 6ኛ ወር Aug 31, 2026 14:43 በጣም ከረዘመ በሥድት ሳምንት የቴሕራን ሥርዓትን መነቃቅሮ ለመጣል፣ የኑክሌር መርሐ-ግብሯን ለመረከብና የአሜሪካ ታማኝ ሥርዓት ቴሕራን ላይ ለመትከል የዋሽግተን-ቴል አቪቭ መሪዎች ለየሕዝባቸዉ የገቡት ቃል ግን በርግጥ በንኗል
ማሕደረ ዜና፣ የ4 ዓመታት ዝግጅት፣የ40 ቀናት ጉባኤ-ለኢትዮጵያ ይበጅ ይሆን?
ማሕደረ ዜና፣ የ4 ዓመታት ዝግጅት፣የ40 ቀናት ጉባኤ-ለኢትዮጵያ ይበጅ ይሆን? Aug 24, 2026 21:56 ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተጠናቀቀዉ ምክክርም ህወሓትን ይዞ፣ ፋኖን፣ ኦነሠን፣ የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ክልሎች አማፂያንን አክሎ፣ ገሚስ-ኦብነግን፣ እንደ ኦነግ፣ ኦፌኮ የመሳሰሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ከሐገር ዉጪ የሚገኙ የፖለቲካ፣ የአካባቢ፣ የመብት ተሟጋቻች ማሕበራትን ጨምሮ አራት አመታት በፈጀዉ የምክክር ሒደት አልተካፈሉም
ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ እብሪት፣ በፍርሐት የተጠፈነገዉ ዓለምና የአፍሪቃ ፈተና
ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ እብሪት፣ በፍርሐት የተጠፈነገዉ ዓለምና የአፍሪቃ ፈተና Aug 17, 2026 14:55 የሆርሙዝ ወሽመጥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ በተለይ አፍሪቃ በማታዉቀዉ፣በማያገባትና በማትፈልገዉ ጦርነት የርዳታ ተመፅዋች ዜጎችዋን ሕይወት እንድትከፍል አስገድዷታል።ከኢትዮጵያ እስከ ናጄሪያ፣ ከሶማሊያ እስከ ሴኔጋል የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የርዳታ እሕል፣ መድሐኒት፣ቁሳቁስ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦባቸዋል
ማሕደረ ዜና፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ የኃይል አሰላለፉ እንዴትነት፣ ምክንያትና መዘዙ
ማሕደረ ዜና፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ የኃይል አሰላለፉ እንዴትነት፣ ምክንያትና መዘዙ Aug 10, 2026 13:03 አፍሪቃ «የራስዋን ችግር በራስዋ መፍታት የመቻሏ» አብነት፣ ኢትዮጵያዉያን እንደሚዋጉት ሁሉ «ለሰላማዊ ዉል ለመገዛትም ፈቃደኛ የመሆናቸዉ» ምሳሌ ተደርጎ ብዙ የተነገረለት የፕሪቶሪያ ሥምምነት ተኩስ ከማስቆሙ እኩል የአዲስ የኃይል አሰላለፍ ምክንያት መሆኑ ነዉ ዚቁ።የተፋላሚ ኃይላት ዋና ተዋኞች በሥምምነቱ ይዘት፣አተረጓጎምና ገቢራዊቱ ላይ ከመነጋገር፣ ለመግባባት ከመጣር ይልቅ አጋር ፍለጋ ሲቃትቱ ከሶስት ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል።
ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉል
ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉል Aug 3, 2026 13:26 ከሰኔ 30 በኋላ ከህወሐት ያፈነገጠዉ አንጃ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጆችና ደጋፊዎቻቸዉን «ጦርነት አንፈልግም» በሚል በአደባባይ ሲያሰልፍ፣ መቀሌ ዉስጥ ደግሞ ህወሓት የጠራዉ ተቃራኒ ህዝባዊ ሥብሰባ ተደርጓል።ስልፍና ስብሰባዉ የቃላት ጦርነቱን ወደየደጋፊዎቻቸዉ ለማስረፅ ያለመ መሆኑ አላከራከረም። የህወሐት ዋና ፀሐፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ለትግራይ ወጣቶች «አሁን ብቻችን አይደለንም» ማለታቸዉ ግን ከቃል አቀባያቸዉ አባባል ጋር የሚጣረስ በተገላቢጦሹ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን ወቀሳ የሚያረጋግጥ ነዉ
ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ጦርነት-አዳዲሶቹ የጦር ግንባሮች
ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ጦርነት-አዳዲሶቹ የጦር ግንባሮች Jul 27, 2026 13:58 የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች፣ የቴሕራኖችን ማስጠንቀቂያ ንቀዉ፣ የዲፕሎማት፣ ተንታኖችን ምክር-ማሳሰቢያ አጣጥለዉ የካቲት 28፣ 2026 ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በስድስተኛ ወሩ ሁለተኛ የዉጊያ ግንባር አስከፈተ። የባብ ኤል መንደብ ወሽመጥን አዘጋም።ሥልታዊዉ ወሽመጥ የአፍሪቃ፣ የእስያና የአዉሮጳ የባሕር መስመር ሕልቅት ነዉ። በባሕር ከሚተላለፉ የዓለም ሸቀጦች ከ12 ከመቶ በላይ ይመላለስበታል።ከዓለም የኢንተርኔት መስመር 17 ከመቶዉ ተዘርግቶበታል።
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዉሳኔ፣የሶማሊያ ሠላምና የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ የመጨረሻ መጀመሪያ
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዉሳኔ፣የሶማሊያ ሠላምና የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ የመጨረሻ መጀመሪያ Jul 20, 2026 14:24 የአሜሪካ ዉሳኔ ከአዉሮጳ ሕብረትና ከፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔዎች ጋር መቃረኑ ዋሽግተኖች ለዉሳኔዉ የሰጡትን ምክንያት አጠያያቂ አድርጎታል።አጠያየቀም-አላጠያየቀ የአሜሪካ ዉሳኔ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ብዙዎች እንደሚሉት 20 ዓመት ግድም ላስቆጠረዉ ለአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ተልዕኮ የመጨረሻዉ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል?
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል? Jul 13, 2026 11:09 የአዲስ አበባና የመቐለ ባለሥልጣናት ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ቢሰጡም በመካከላቸው ያለው እሰጥ አገባ ከፍተኛ ዕልቂትና ብርቱ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዳያገረሽ የሚያሠጋ ነው። በጥቅምት 2013 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ወደ ድርድር ለመግፋት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አስፈልጓል።
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብ
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብ Jul 6, 2026 15:16 ከዓለም ምጣኔ ሐብት 23 ከመቶዉን ያክል የምትቆጣጠረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ።ዩናይትድ ስቴትስን በሩቅ ርቀት የምትከተለዉ ቻይና፣ ቻይናን እጅግ በጣም ርቃ የምትከተለዉ ጀርመንና ከጀርመን የምትቀጥለዉ የጃፓን ኤኮኖሚ ቢደመር የአሜሪካንን አያክልም።ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ ሊግ ኦቭ ኔሽንስን አፍርሳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በሚጠቅማትና ዓላማዋን በሚያራምድ መልክ አደራጅታለች።
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉዝግብ፣ የአረቦች ሥልትና የቀይ ባሕር መዘዝ
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉዝግብ፣ የአረቦች ሥልትና የቀይ ባሕር መዘዝ Jun 29, 2026 13:51 የዋሽግተንና የቴሕራን ቁርቁስ፣ በቴል አቪቭ-ቤይሩቶች ደባ ላይ ታክሎ እንጭጩን ሥምምነት እንድም ሆርሙዝ ሰርጥ አለያም ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ እንዳያሰምጠዉ ሲፈራ-ሰሞኑን፣ ቀይ ባሕር መስመር የአዲስ ሽኩቻ-ሽሚያና ግጭት መድረክ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።አል ቁዱስ የተባለዉ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር (IRGC) ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጌድየር ጄኔራል እስማኢል ቃኒ ሐገራቸዉና ተባባሪዎችዋ አዲስ የፀጥታ መቀነት መዘርጋታቸዉን ሲናገሩ የሰማ እንጂ ያመናቸዉ ጥቂት ነበር።

Empfohlen