
ማሕደረ ዜና
ማሕደረ ዜና በየሳምንቱ ሰኞ የሚቀርብ የዜና ትንታኔ ፖድካስት ነው። በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የተከሰቱ፣ የሚከሰቱ እና የተነገሩ ዋና ዋና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ዝግጅቱ የሀገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማህበራትን፣ ድርጅቶችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት ተግባራትን በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ያቀርባል። አዘጋጁ ነጋሽ መሐመድ ነው።
Folgen

የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል?
የአዲስ አበባና የመቐለ ባለሥልጣናት ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ቢሰጡም በመካከላቸው ያለው እሰጥ አገባ ከፍተኛ ዕልቂትና ብርቱ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዳያገረሽ የሚያሠጋ ነው። በጥቅምት 2013 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ወደ ድርድር ለመግፋት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አስፈልጓል።

ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብ
ከዓለም ምጣኔ ሐብት 23 ከመቶዉን ያክል የምትቆጣጠረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ።ዩናይትድ ስቴትስን በሩቅ ርቀት የምትከተለዉ ቻይና፣ ቻይናን እጅግ በጣም ርቃ የምትከተለዉ ጀርመንና ከጀርመን የምትቀጥለዉ የጃፓን ኤኮኖሚ ቢደመር የአሜሪካንን አያክልም።ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ ሊግ ኦቭ ኔሽንስን አፍርሳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በሚጠቅማትና ዓላማዋን በሚያራምድ መልክ አደራጅታለች።

ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉዝግብ፣ የአረቦች ሥልትና የቀይ ባሕር መዘዝ
የዋሽግተንና የቴሕራን ቁርቁስ፣ በቴል አቪቭ-ቤይሩቶች ደባ ላይ ታክሎ እንጭጩን ሥምምነት እንድም ሆርሙዝ ሰርጥ አለያም ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ እንዳያሰምጠዉ ሲፈራ-ሰሞኑን፣ ቀይ ባሕር መስመር የአዲስ ሽኩቻ-ሽሚያና ግጭት መድረክ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።አል ቁዱስ የተባለዉ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር (IRGC) ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጌድየር ጄኔራል እስማኢል ቃኒ ሐገራቸዉና ተባባሪዎችዋ አዲስ የፀጥታ መቀነት መዘርጋታቸዉን ሲናገሩ የሰማ እንጂ ያመናቸዉ ጥቂት ነበር።

ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ
ከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል።

ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ
ከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል።

ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ሥምምነት-የሠላም ጭላንጭል ብርቀት
ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ሆነዉ ኢራን ላይ ጦርነት የከፈቱት ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንኔታንያሁ በድርድሩ ሒደ,ት አልተሳተፉም ወይም ተገልለዋል።የእስራኤል የባር ኢላን ዩኒቨርስቲ የፖለካ ሳይቲስት ዮናታን ራይንሆልድ እንደሚሉት ሥምነቱ ለጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ፖለቲካዊ ሕይወት መጥፎ ነዉ።ኔታንያሁ አሁን የሚመኙት ተንታኙ እንዳሉት ጦርነቱ እንዲቀጥል ነዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የድርድር መሐል ጦርነት፣ የጦርነት መሐል ድርድር---ዜሮ ዉጤት
በአሜሪካ አማላጅነት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ ሶስቴ ተኩስ እንዲቆም ከእስራኤል ጋር ተስማምቶ ነበር።ደቡባዊ ሊባኖስን የሚያወድመዉ የእስራኤል ጦር ድብደባ ወይም ጦርነት-ይባል ግጭት የመጫሩ ምክንያት በኢራን ላይ ጦርነት በመከፈቱ ከሆነ የኢራኑ ጦርነት ሲቆም የሊባኖሱ ያልቆመበት ምክንያት ከተጠየቀ-ትክለኛዉ መልስ «በጡንቻዉ የታበየን ማንጠይቆት» የሚል ነዉ-የሚሆነዉ።እንዲያዉ ለማለቱ ያክል ሒዝቦላሕና እስራኤል እየተዋጉ፣ የሒዝቦላሕ ጠላት እስራኤልና የሒዝቦላሕ ተቃዋሚ የቤይሩት መንግሥት፣ በሒዝቦላሕ ጠላት፣ በእስራኤል ጥብቅ ወዳጅ ዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት «ግጭትን ለማቆም» ተብዬዉን ስምምነት መዋዋላቸዉ---

ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ይደራደራሉ፣ ይግባባሉ፣ ይዛዛታሉም
ባለፈዉ ቅዳሜም የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት ለዓለም ነጋዴ «እንቁልልጭ» በማለታቸዉ የነዳጅ ዘይት ዋጋ እንዲያሽቆለቁል አድርገዋል።እዉነቱ ግን «ባጭር ጊዜ» በይፋ ይደረጋል ያሉት ሥምምነት ቅዳሜም አልነበረም ዛሬም የለም።ወይም የአጭር ጊዜ ብያኔ አይታወቅም።ትራምፕ በመሐሉ ትናንት በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሰራጩት መልዕክት ኢራን ካልተስማማች ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ወደቦች በሚነሱ መርከቦች ላይ የጣለችዉን እገዳ እንደማታነሳ ዝተዋል።

የኢትዮጵያ እና ሱዳን ፍጥጫ ወዴት እያመራ ነው?
የሱዳን ብሔራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚያደርጉት ውጊያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ወደሚገኝበት ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የበለጠ በመጠጋት ላይ ይገኛል። የሱዳን ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር “የሁለትዮሽ መዋቅራዊ የውይይት ማዕቀፍ” ሥምምነት የተፈራረመችው አሜሪካ በዐይነ-ቁራኛ የምትከታተለው ነው። አሜሪካ ግንቦት 24 ቀን 2018 ይካሔዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ምርጫ በኋላ ኢትዮጵያ እና ግብጽን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ማደራደር ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ጦርነት እንዲቀሰቀስ እንደማትሻም አስታውቃለች።

ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስ-እስራኤልና ኢራን በጦርነትና ዲፕሎማሲ መሐል
ለኔታንያሁ ሰበብ ሆኑ ትክክለኛ ምክንያቶች ሐመስ፣ ሒዝቦላሕ፣ሁቲ ጭፍራ፣ ኢራን ዋና የሽብር ማዕከል ናቸዉ።የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች ዋና ጠላት የሚሏትን ኢራንን ለማንበርከክ አምና ሰኔ ሞክረዋታል።አልተሳካም።ዘንድሮ ከየካቲት ማብቂያ እስከሚያዚያ ቀጥቅጠዋታል። የትራምፕ-ኔታንያሁ ዕቅድ፣ፉከራ፣ ዛቻ ምናልባት አንዳዶች እንደሚሉት ለሽንፈት እንጂ ለድል አልበቃም።7000 ዘመናት ያስቆጠረዉን የኢራንን ሥልጣኔ ለማዉደም ትራምፕ ፎክረዉም ነበር።አልቻሉም።

የትግራይ ክልል አዲስ ፕሬዝደንት አዲስ ሥራ አስፈጻሚ እየጠበቀ ነው-ግጭት የማቆም ሥምምነቱስ?
በህወሓት ውሳኔ መሠረት በጳጉሜ 2012 በተካሔደው እና ፌድራል መንግሥት “ሕገ-ወጥ” ባለው ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በመጪዎቹ ቀናት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ ወደ ሥራ መመለስም ይሁን የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የትግራይ ክልል እና የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ቀጣይ ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሚበይኑ ይሆናል።

የሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ማኅደረ ዜና

ሱዳን “የጭካኔ ቤተ-ሙከራ” የሆነችበት ጦርነት አራተኛ ዓመቱን ጀመረ
በሱዳን ጦርነት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድሮኖች ጥቃት ጭምር ተገድለዋል። ጦርነቱ አራተኛ ዓመቱን ሲጀምር 34 ሚሊዮን ሰዎች ሰብአዊ ርዳታ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱን ለሁለት የከፈላትን ጦርነት ለማቆም የሚደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ጦርነቱ ከሱዳን ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተዛምቶ “ከቁጥጥር ውጪ” ሊሆን እንደሚችል ሥጋት አለ። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አዛዥ ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጦርነቱን ለማቆም እስካሁን ተጨባጭ ፈቃደኝነት አላሳዩም።

ድርድሩ ከሽፏል ፤ ጦርነቱ ያገረሽ ይኾን ?

ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ ስድብና ዛቻ፣ ያበደዉ ማን ይሆን?
የኢራን ትምሕርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የመድሐኒት ፋብሪካዎች፣ ድልድዮች፣ ዩኒቨርስቲዎች ሳይቀሩ ወድመዋል።የእስራኤልና የመካከለኛዉ ምሥራቅ የአረብ ሐገራት በርካታ የኃይልና የሰላማዊ ተቋማት ተመትተዋል።ከሁሉም በላይ ምትክ የሌለዉ ከአራት ሺሕ በላይ ህይወት ጠፍቷል።በአንዳዶች ግምት በትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አንድም ጠፍቷል ሁለትም ከስሯል።ትራምፕም ግን ነገ ማክሰኞ የኢራን የመሰረተ ልማት ተቋማት የሚፈራርሱበት ቀን እንደሆነ አዉጀዋል።ባለፈዉ ሳምንት ለኢራኖች የሚገባዉ «የድጋይ ዘመን ነዉ» ያሉት ትራምፕ ትናንት ኢራኖችን «እብድ፣ ዲቃሎች» በማለትም ባደባባይ ተሳድበዋል።ያበደዉ ማን ይሆን?

የነዳጅ እጥረት ያስከተለው ቀውስ እና ኢትዮጵያ ልትከተለው የሚገባ ዘላቂ ስልት

እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት እንዴት እና መቼ ይቆማል?
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሣምንት አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት መቼ እንደሚቆም ሲጠየቁ “እስከ አጥንቴ ዘልቆ ሲሰማኝ” የሚል መልስ ሰጥተዋል። መልሳቸው የጦርነቱን መቋጫ ለሚናፍቁ ማስተማመኛ የሚሰጥ አይደለም። ተንታኞች 24ኛ ቀኑን ያስቆጠረው ጦርነት የሚቆምበት ጊዜ እና ሁኔታ እጅግ ውስብስብ እንደሆነ ሥጋት አላቸው።

ማሕደረ ዜና ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን የዉጊያ ሥልትና መልስ የለሽ ጥያቄዎች
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መንግሥት ኃይለማርያም የናደዉ ዕዝ በ1987 (እጎአ መሆኑን አይዘንጉ) ግድም አፍአበት ላይ የገጠመዉን ሽንፈት ጠላት «አካቢዉን ከበቦ ሲያበቃ የዕዙን ጭንቅላት በጠበጠዉ» ዓይነት ብለዉ ባጭሩ ገልፀዉት ነበር።የእስራኤልና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የካቲት 28 ጧት የኢራንን የፖለቲካ፣ የጦርና የስለላ እናትን ቆርጦ ቢጥልም ፋርሶች እንደታሰበዉ «ያልተበጠበጡበት» ሁለተኛዉ ምክንያት የጠላታቸዉን የዉጊያ ሥልት ብዙ አጥንተዉ በቅርብ አመታት ኢራቅ፣ አፍቃኒስታንና ሊቢያ ላይ ከሆነዉ ተምረዉ የነኬይን ዘመናይ ሥልት በነ አፄ ምኒልክ ጥንታዊ ሥልት ለመመከት በመዘጋጀታቸዉ ነዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ያስከተለዉ ምሥቅልቅል
እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን መደብደብ የጀመሩት ቴሕራን ላይ የኢራን መሪዎችን፣ ሚናብ ዉስጥ ሕፃናት ሴት ተማሪዎችን በመግደል ነዉ።መሪዎቹን ከነሚስት ልጆቻቸዉ መግደል ለቴል አቪቭ ዋሽግተን መሪዎች ራሳቸዉ ደጋግመዉ እንዳሉት ጀግንነት ነዉ።የሚናብ-ኢራን ሴት ተማሪ-አስተማሪዎችን መግደል ግን ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራም የቴሕራኖች ሥራ እንጂ በዓለም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጦራቸዉ ስሕተት ዓይደለም።

ማሕደረ ዜና፣ የኻምኔይ መገደል፣ የኔታናያሁ የዕድሜ ልክ ምኞትና የትራምፕ ፉከራ
ሳዳም ሁሴይ፣ ኦስማ ቢን ላደን፣ ሙዓመር ቃዛፊ፣ ዑስማኢል ሐንያሕ፣ ሐሰን ነስረላሕ ሌሎችም ሲገደሉ ዓለም ከአምባገነኖች፣ከጨቋኞች እና ካሸባሪዎች መላቀቋን የቴል አቪቭ-ዋሽግተን-ለንደን-ብራስልስ መሪዎች ለዓለም አዉጀዉ ነበር።ዓለም ግን ዘንድሮም ሰላም አታዉቅም።አምና ጥር ለሁለተኛ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስን የፕሬዝደትነት ሥልጣን የያዙት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ፕሬዝደንት መሆናቸዉን ሲደሰኩሩ የልዕለ ኃያሊቱ ሐገር መሪዎች የጦርነትን አትራፊነት ብቻ ሳይሆን አስከፊነትቱን የተረዱ መስለዉ ነበር

ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት አራተኛ ዓመት፣ መቆሚያ አለዉ ይሆን?
ዩክሬንን የሚደግፉት የምዕራባዉያን መንግሥታትና ተቋማት እንደሚሉት የሩሲያ ዕቅድ ኪቪን ባጭር ጊዜ ምናልባትም በሶስት ቀናት ዉስጥ ተቆጣጥሮ ዜለንስኪና ተባባሪዎቻቸዉን አንቆ ወደ ሞስኮ ለመዉሰድ ነበር።ፑቲን ግን ዘመቻዉ ልዩ፣ ዩክሬንን በኃይል የመግዛት ዕቅድም እንደሌላቸዉ አስታዉቀዉ ነበር።የጦርነቱ ዕቅድ ምዕራባዉያኑ እንደገመቱትም ሆነ ፑቲን እንዳሉት እስካሁን አሸናፊና ተሸናፊ አልተለየም።

ማሕደረ ዜና፣62ኛዉ የሙኒክ የፀጥታ ጉባኤ፣የአዉሮጳ አሜሪካኖች ልዩነት መድረክ
የጀርመኑ መራሔ መንግሥት የአሜሪካ ወዳጆቻችን በቀጥታ እንዲረዱት በማለት ለጉባኤተኞች በእንግሊዘኛ ጭምር ያደረጉት ንግግር አዉሮጶች በትራምፕ አስዳደር እርምጃና መርሕ ከመስጋት አልፈዉ መናደድ፣ መቆጣታቸዉን የሚያስረዳ ነዉ።የፈረንሳይና የሌሎች የአዉሮጳ መንግሥታት መሪዎችና ተወካዮችም የፕሬዝደንት ትራምፕ አስተዳደርን በተደጋጋሚ ተችተዋል።አዉሮጳ የራስዋን የመከላከያ ኃይል ማጠናከር እንደሚገባት አሳስበዋልም።

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ኤርትራ ጠብ፣ የአፍሪቃ ቀንድ የሰላም ሥጋት
ሮሞች፣ቱርኮች፣ፖርቱጋሎች፣ አረቦች፣ አዉሮጶች፣ሐበሾች፣ ግብፆች፣ ሶቭየት ሕብረቶች፣ ኩባዎች፣ አሜሪካኖች በየዘመናቸዉ ዘምተዉ ገድለዉ ሞተዉበታል።የዚያን ምድር ሕዝብ ደም አፋሰዉበታል።በቅርቡ ደግሞ የመካከለኛዉ ምሥራቅና የእስያ ኃያል ቱጃር መንግሥታት እየተራኮቱበት ነዉ።የአፍሪቃ ቀንድ።የጎቲንገን ዩኒቨርስቲ ባልደረባ ዶክተር ማርኩስ ፊርግል ሆነ እንደሚሉት የአፍሪቃ ቀንድ የአዲስ ቅርምትና ማዕከል ሆኗል።

ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፍጥጫ ዲፕሎማሲ ወይስ ዉጊያ
ባለፉት ጥቂት አመታት የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች በወሰዱት እርምጃ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከልነቱ የተሽመደመደዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዲፕሎማቶችም የዋሽግተንና የቴሕራን መሪዎች ጦርነት ከመግጠም እንዲታቀቡ አደራ ብለዋል።በለንደን ስኩል ኦፍ ኤኮኖሚክስ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ፋዉዝ ጀርጀስ እንደሚሉት የዲፖሎማሲ ጥረት እየከሰመ፣ የጦርነቱ አይቀሬነት እየደመቀ ነዉ።

ማሕደረ ዜና፣ አንድ ዓመት ከትራምፕ «አሜሪካ ትቅደም» መርሕ ጋር
የምዕራብ አዉሮጳ መንግሥታት የእስራኤን አለመቃወማቸዉን ሲያስታዉቁ፣ ትራምፕ እስራኤልን ደግፈዉ ኢራንን ደበደቡ።ኢራንን የኑክሌር ተቋማት ሙሉ በሙሉ አወደምን አሉም።12 ቀናት ያስቆጠረዉ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት በተለይ ኢራንና እስራኤል ዉስጥ የሰዉ ሕይወት ከማጥፋቱ በተጨማሪ ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት ኪሳራ አስከትሏል።ዩናይትድ ስቴትስም ለ18 ሰዓታት ድብደባ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር አዉጥታለች።የ12ቀናቱ ድብደባማ ሆነ ትራምፕ ያወ,ጁት ድል የእስራኤል፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን መሪዎች ለተጨማሪ ጦርነት ከመዛዛት፣ በጦር ኃይል ከመፋጠጥ አለማዳኑ እንጂ እንቆቅልሹ።ፍጥጫዉ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።

ማሕደረ ዜና፤ ሶማሊያ፣ የአዲሱ የአፍሪቃ ቀንድ ቅርምት ማዕከል
በማግሥቱ ቅዳሜ የሞቃዲሾ መንግሥትን የሚደግፉ ወይም የእስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን እርምጃ ከሚቃወሙት መካከል የቱርክ፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ የሱዳንና የጅቡቲ አምባሳደሮችና ፖለቲከኞች ላስ አኖድ ገቡ።የዲፕሎማቶቹና የፖለቲከኞቹ ጉብኝት አዲስ በተመረጡት የሰሜን ምሥራቅ ግዛት ፕሬዝደንት አብዲቃድር አሕመድ አዊ-ዓሊ (ፊርዲሕዬ) በዓለ-ሲመት ላይ ለመገኘት እንደሆነ ተነግሯል።ትክክለኛ መልዕክቱ ግን እስራኤል ከድፍን ዓለም ተሽቀዳድማ፣ የዓለም ሕግን ጥሳ፣ የሶማሊያን ሉዓላዊነት አፍርሳ፣ ለሶማሊላንድ ዕዉቅና መስጠቷን ከቃላት በላይ በድርጊት ለመቃወም ነዉ

ተቃውሞ የበረታባት ኢራን ለድርድርም ይሁን ለጦርነት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
ኢራን ዳግም በተጣለባት ማዕቀብ መገበያያ ገንዘቧ ሲላሽቅ በተፈጠረ ኢኮኖሚያዊ ጫና የተቀሰቀሰ ተቃውሞ ሦስተኛ ሣምንቱን አስቆጥሯል። እስካሁን ከ530 በላይ ተዋሚዎች እና የጸጥታ አስከባሪዎች መገደላቸውን አክቲቪስቶች ገልጸዋል። ኢራን ለተቃውሞዎች እንግዳ ባትሆንም ጂዖ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል መሪዎች የሰጧቸው አስተያየቶች የአሁኑን አሳሳቢ አድርገውታል።

የታኅሳስ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ማኅደረ ዜና

የእስራኤል ዕውቅና መስጠት ይቀለበስ ወይስ ሌላ ተከታይ ያፈራ ይኾን?

የታኅሳስ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ማኅደረ ዜና

ማኅደረ ዜና፤ ውጥረት ያልተለየው የአፍሪቃ ቀንድ ወቅታዊ ኹኔታ

ሶሪያ፤ አንድ አመት ክበሺር አላሳድ በኋላ

የደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ያየለበት የቡድን 20 ጉባኤ
የቡድን 20 ጉባኤ ሲጠናቀቅ በሱዳን፣ ኮንጎ፣ በእስራኤል በጉልበት በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶችና በዩክሬን “ፍትኃዊ፣ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ሰላም” እንዲወርድ እንደሚሠሩ መሪዎቹ ቃል ገብተዋል። በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደው ጉባኤ የደቡብ አፍሪካ እና የአሜሪካ ውዝግብ ተጭኖታል። ጉባኤው ሲጠናቀቅ አሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝደንትነቱን አልተረከበችም።

ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ ተቃራኒ የአፍሪቃ መርሕ
አንዳዶቹ ፎቶ ግራፎች ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዉስጥ የተነሱ መሆናቸዉ ቢረጋገጥም የነጮችን የበላይነት ለማስከበር ቆርጠዉ የተነሱት ዶናልድ ትራምፕ ግን ነጭ ደቡብ አፍሪቃዉያን ወደ አሜሪካ እንዲሰደዱ ፈቀደዋል።አሜሪካ ጥግ የምትገኘዉን የጃማይካ ስደተኛን ሳይቀር ከአሜሪካ ወደ አፍሪቃ ያስግዛሉ።መሰደድ የማይፈልጉትን የደቡብ አፍሪቃ ነጭ ዜጎችን ወደ አሜሪካ ይጋብዛሉ።ከአፍሪቃ ጋር የንግድ ግንኙነትን ማጠናቀር እሻለሁ ይላሉ፤ ደቡብ አፍሪቃን በዘረኝነት ያወግዛሉ።

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ምድር ሌላ ጦርነት እየተደገሰለት ይሆን?
ኢትዮጵያ በየሥፍራዉ ከሚደረጉ ግጭቶች በተጨማሪ የኑሮ ዉድነት፣ ሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ደሕንነት እጦት፣ እገታና ግድያን የመሳሰሉ የሕግና ሥርዓት መጓደሎች አቃርጠዉ እንደያዟት ነዉ።ትግራይን ጨምሮ ከአራት ሚሊዮን የሚበልጥ ተፈናቃይ በየመጠለያ ጣቢያዉ እንደሰፈረ ነዉ።የኤርትራ ሁኔታም ከኢትዮጵያ የባሰ እንጂ ያነሰ አይደለም።በዚሕ ላይ አካባቢዉ ሌላ ጦርነት ይችል ይሆን?

የማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
ፓሪስ፥የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ያስተዋወቀ መድረክ ተከናወነ፣ ዴንሐግ፥ በሰዎች ማዘዋወር የተጠረጠረ ኤርትራዊ ላይ ኔዘርላንድስ ውስጥ ክስ ተከፈተ፣ ካርቱም፥ የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ለዕርቅ አወንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን የትራምፕ ረዳት ተናገሩ፣ ዳርኤሰላም፥ ፖሊስ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች የሚረብሹ ምስሎች እንዳይጋሩ አስጠነቀቀ፣ ቤርሊን፥ ጀርመን በሚቀጥለው የጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2026 ለዩክሬይን የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለማሳደግ ወሰነች

ማሕደረ ዜና፣ ኤል ፋሻር-የሱዳን እልቂት አዲስ ምዕራፍ
የካይሮና የአቡዳቢ ገዢዎች የመንንን ለመደብደብ ጥብቅ ወዳጅ ነበሩ።ቀጠር በማዕቀብ ለመቅጣት ተባባሪ ነበሩ።የቀድሞዉን የሶሪያ መሪ በሽር አል አሰድን ለማስወገድ ተመሳጣሪ ነበሩ።ሱዳንና ሊቢያ ጦርነት ላይ ተቃራኒ ኃይላትን ይደግፋሉ።ሱዳንም የቀድሞ ወዳጆች የገጠሙት-ወዳጆችን ያቃረነ ጦርነት ማዕከል እንደሆነች ቀጥላለች።

ማሕደረ ዜና፣ የASEAN ጉባኤ፣ የትራምፕ ጉብኝትና የሲኖ-አሜሪካ ድርድር
ቤጂንጎች ሲያመሩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ «የንግድ ጦርነት ቀላል ነዉ አልኩ እንጂ---ከቻይና ጋር ማለቴ አልነበረም» ማለታቸዉ ተዘገበ።ዘ-ኤኮኖሚስት የተሰኘዉ መፅሔት ደግሞ በቀደም «ቻይና በትራምፕ ዱላ አሜሪካናንን ደበደበች» አለ።የሁለቱ ሐገራት የንግድና የኤኮኖሚ ባለሥልጣናት ሰሞኑን ለ5ኛ ዙር እየተደ,ራደሩ ነዉ።የቻይና ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጉዮ ጂያኩን ዛሬ እንዳሉት ዉይይቱ የሰከነና መግባባት የታየበት ነዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ሶማሊላንድ ጥልፍልፍ
የኢሮ ጉብኝት ባለፈዉ ሐሙስ ሲጠናቀቅ የበርበራ ወደብን የሚገነባዉ፣ DP ወርልድ የተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያ፣ መርከቦች ከርበራ ወደብ ጀበል ዓሊ ወደተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወደብ እና በተቃራኒዉ መጓዝ መጀመራቸዉን አስታዉቋል። በኢትዮጵያ-ሶማሊያና ሶማሊላንድ መሪዎች ጉብኝት፣ ዉይይት፣ የፖለቲካ ጥልፍልፉ የአቡዳቢና የካይሮ ገዢዎች በቀጥታም በተዘዋዋሪም ጫና ማድረጋቸዉ የተሠወረ አይደለም።ይሁንና የሶማሊላንድ ዲፕሎማቶች በግል እንዳሉት ኢሮ የመሩት የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ በኩል የቀረበለትን የሶማሊያ ፕሬዝደንትን ሥልት አልተቀበለዉም።ጉብኝቱም ባጭሩ ተጠናቅቋል።ምናልባት እስከሚቀጥለዉ ጊዜ።

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?
ኢትዮጵያ ዘንድሮ የሕዳሴ ግድብን አስመርቃለች።፣የካሉብ ጋዝ ማምረቻና የማደባሪያ ፋብሪካን የመሠረት ድንጋይ ጥላለች።አማራ ክልል ከፋኖ፣ ኦሮሚያ ክልል ከኦነሠ ወይም OLA ጋር የሚደረገዉ ዉጊያ አሸናፊና ተሸናፊ ሳይለይበት እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያ ምናልባትም የኤርትራ ክረምት ግን አብቅቷል።ዓየሩ ለወታደራዊ ንቅናቄ ይመቻል።እና ይዋጉ ይሆን?

ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል መጠቃት፣ የጋዛ ጦርነትና ድርድር 2ኛ ዓመት
ሕዝባቸዉ በየአደባባዩ የሚያደርገዉ ግፊት የጠናባቸዉ የምዕራብ አዉሮጳ መሪዎች እየተግተለተሉ ለፍልስጤሞች የመንግሥትነት እዉቅና ሰጡ።ኔታንያሁ በሚጭሩት ጦርነት ዘለዉ በመግባት ወይም ለኔታንያሁ መንግስት ፍፁም ድጋፍ በመስጠታቸዉ ምክንያት አረብ-ሙስሊም እየራቃቸዉ፣ ሕዝብ እየተከፋባቸዉ፣ ከተቀረዉ ዓለምም እየተነጠሉ የመጡት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥብቅ ወዳጃቸዉን ኔታንያሁን በቅርቡ «በቃሕ» አሉሏቸዉ።ወይም ያሉ መሰሉ።

ማሕደረ ዜና፣ ዓለም መሪዎች እየተግባቡ ይሆን ወይስ ግራ እያጋቡ
ሰዉዬዉ ከመቸኮላቸዉ የተነሰ በእስራኤል ላይ የሚለዉን በኢራን ላይ የተቃጣ አደጋ ብለዉት ነበር።ቸኩለዉ አሉት።ፈጥነዉ አረሙት።ኔታንያሁ እስራኤል ከመጥፋት አደጋ፣ ዓለምም ከመገደል ሥጋት ድኗል ቢሉም የለንድን፣ የፓሪስና የበርሊን መሪዎች አልተቀበሉትም። እንደ አሜሪካ ሁሉ የእስራኤል የቅርብ ወዳጆች፣ የኢራን ጠላቶች ፈረንሳይ፣ ብሪታንያና ጀርመን የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር ያሰደረዉ ሥጋት አልተወገደም ይላሉ።ወይም የኔታንያሁን ማረጋገጪያ አላመኑትም።በሶስቱ ሐገራት ግፊት የተሰየመዉ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኢራን ላይ ዳግም ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣል ወስኗል።

ማሕደረ ዜና፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ80 ዓመት አዛዉንት ወይስ ጨቅላ?
ዓለም ከአንድ ሐገር የአዉቶሚክ ሥጋት ወደ ዘጠኝ ሐገራት የኑክሌር ሥጋትና ፍጥጫ ያደገችበት 80 ዓመት የሰላም ዘመን ነበር ማለት ይቻል ይሆን? አንዳድ ጥናቶች እንደጠቆሙት የጋራ ማሕበር ከተመሠረተ ከ1945 ወዲሕ ዓለም ከ300 በላይ ከባድ ጦርነቶችን አስተናግዳለች።በአብዛኞቹ ጦርነቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች፣ የዓለም ልዕለ ኃያላን መንግሥታት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ተካፍለወል።----ዛሬም ከሱዳን እስከ ጋዛ፣ ከዩክሬን እስከ ኮንጎ ዴምክራቲክ ሪፐብሊክ ዓለም ሰላም የላትም

ማሕደረ ዜና፣ ዝክረ-2017 ዓበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች
2017 ኤርትራን፣ ሶማሊላንድን፣ ሶማሊያንና ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር አስማማም-አጣላ፣ ቱርክን ለሽምግልና ጋበዘም-ጣልቃ አስገባ፣ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ እስከ አዲስ አበባ ኢትዮጵያዉያንን አስደሰተም-አስከፋ ሰበብ ምክንያቱ ሁለትም-አንድም ነዉ ወደብና ግድብ።ዉኃ።በ2017 የኮሪደር ልማትን አዲስ አበባ ላይ ክፉኛ የተፈተነዉ ጎርፍ ነዉ።-ዉኃ፣ወለጋና ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በትንሹ 10 ሰዎችን የገደለዉ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ላይ ሺዎችን ያፈናቀለዉ፣ ደቡብ ወሎ ዉስጥ የተፈናቃዮችን መጠለያ ጣቢያ ያጠፈዉ ጎርፍ ነዉ-ዉኃ።ሥደተኞችን የበላዉ-ባሕር ነዉ።ዉኃ።

የኦሮሚያ የጸጥታ ኹኔታ እና የአዲሱ ዓመት መባቻ
ዓመታትን ያስቆጠረው የትጥቅ ትግል አሁንም ድረስ መቋጫ አላገኘም ። አንዴ ውጥረት እያነገሰ ሌላ ጊዜ ረገብ እያለ የቀጠለው የታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ አካላት ግጭት ለማህበረሰቡ ሌላ ስጋት ካስከተለ ሰነበተ ። ዕገታ ፤ የዘፈቀደ ግድያ እና ዘረፋ ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው ።

የነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና፣የኢትዮጵያ ጉዞ አቅጣጫዉ ይታወቅ ይሆን?
ኢትዮጵያ ከሉሲ ግኝት እስከ አክሱም ሐዉልቶች፣ ዋልያን ከመሰሉ-እንስሳት እስከ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ከሶፍ ዑመር ዋሻ-እስከ ሐረር ግንብ፣ ከአድዋ እስከ ካራማራ ድል የሚደርሱ የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የተፈጥሮ ፀጋ፣ የጀግንነት ታሪኮች ባለቤት መሆንዋ አያከራክርም።የዚያኑ ያክል የርስበርስ ጦርነት፣ የጎሳ ጥቃትና የፖለቲካ ዉዝግብ ኢትዮጵያን ቁል ዉል እየደፈቋት ነዉ።የድሕነት፣የበሽታና የረሐብ አስከፊነት ከተጠቀሰ የኢትዮጵያዉያን ቁጥር የአሐዞች ማድመቂያ ነዉ።የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣የስደተኞች ብዛትና ሞት ከተዘረዘረ ኢትዮጵያና ዜጎችዋን ማለፍ አይቻልም።ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታና ዘረፋም ከኢትዮጵያ «መለያዎች» እየተካተቱ ነዉ

ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት፣የጉባኤ ጋጋታና የዲፕሎማሲዉ ዉጣ ዉረድ
3 ዓመት ከመንፈቅ።ጦርነቱ አንዳዶች እንደገመቱት ከሁለቱም ወገን በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ወታደር አልቆበታል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሠላማዊ ሰዉ ተገድሏል።ቆስሏል።ተፈናቅሏልም።በብዙ መቶ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሐብት ንብረት ወድሟል።ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአዉሮጳ ሕብረትና ብሪታንያ ከመቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስክሰዋል።ያሸነፈም፣ የተሸነፈም የለም።የጦርነቱ መሠረታዊ ምክንያት ምንም ሆነ ምን ከግዛት ይገባኛል ያለፈ ሰበብ አልቀረበበትም።ተጨማሪ ሕይወት፣ ሐብትና ንብረት እንዳይጠፋ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈዉ ቅዳሜ አንዳሉት ተፋላሚዎች ሰጥቶ ለመቀበል ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል።

ማሕደረ ዜና፤ የጋዛ እልቂት፣ የእስራኤል አዲስ ዕቅድና የገጠመዉ ተቃዉሞ
በእስራኤልና በጠላቶችዋ አፀፋ ጥቃት ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ፣ ቤይሩት፣ ሐይፋ፣ ቴሕራን፣ ብዙ ሺሕ ሕዝብ አልቋል።የጋዛ ለብቻዉ ነዉ።የግዛቲቱ የጤና መስሪያ ቤት እንዳስታወቀዉ ከ60ሺሕ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።ረሐብ የፈጀዉ ሰዉ ቁጥርም ወደ ሁለት መቶ ተቃርቧል።ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል።እስራኤልም ወደ 800 የሚሆኑ ወታደሮች ተገድለዋባታል።22 ወራት።ከዚሕ ሁሉ እልቂት፣ስደት፣ረሐብ፣ ስቃይ-ሰቆቃ፣ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ዕቅድ ከግብ አልደረሰም።

ማሕደረ ዜና፣ ሒሮሺማ-የመጀመሪያዋ የአዉቶሚክ ቦምብ ሰለባ 80ኛ ዓመት
«ያየነዉን ማመን በጣም ከባድ ነበር።» አሉ ኮሎኔል ቲቤትስ ኋላ።«አንዱ ባልደረባችን «የፈጣሪ ያለሕ» ሲል ሰማሁት» አከሉ ኮሎኔሉ።እነሱ የሚጥበረብር አስደንጋጭ ብልጭታ፣ ሰቅጣጭ-ድምፅ፣ ሐምራዊ፣ሰማያዊ ነጭ ቀለም ያለዉ ወፍራም፣ እምቅ፣ ጢሱን ሰንጥቀዉ ወደ መጡበት ተፈተለኩ።መሬት ላይ ለነበሩት ግን የዕልቂት እቶን በር ተበረገደ።አፍንጫ የሚሰነፍጥ ቅርናት፣ጆሮን የሚሰቀጥጥ የሰቆቃ ጩኸት፣ ከተቀመጡት አስፈንጥሮ የሚያንሳፍፍ ንዝረት፣ ትንፋሽ የሚያሳጣ ወበቅ---ዕልቂት።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሐሪስ ኤስ ትሩማን እንዳሉት ግን ለዩናይትድ ስቴትስና ለተባባሪዎቿ ታላቅ የታላቅ ድል የመጀመሪያ ምዕራፍ ነዉ

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ ማብቂያ ያገኝ ይሆን?
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሥልጣን የያዙ ይሁኑ ተቃዋሚዎች ምንም አሉ-አደ,ረጉ፣ግጭት፣ጥቃት፣ ግድያ፣ እገታ፣ዘረፋና ስርዓተ አልበኝነት ግን ለኢትዮጵያዉያን የአዘቦት ትርዒት እስኪመስል ድረስ እንደቀጠለ ነዉ።የመንግሥት ባለሥልጣናትና ደጋፊዎቻቸዉ የቀዉሱን ንረት፣የሚያደርሰዉን ጥፋትና ምናልባት መፍትሔዉን የሚነግሯቸዉን ሁሉ የዚሕ ወይም የዚያ ጎሳ፣ ቡድንና ፓርቲ አባል እያሉ ከመፈረጅ ባለፍ እስካሁን መፍትሔ መስጠት አልቻሉም።ወይም አልፈለጉም።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት፣ ግጭት፣ ጥቃትና ምሥቅልቅሉ ኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉ ጥፋት፣ አልበቃ ያለ ይመስል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሐገራት ጋር የገጠመችዉ አተካራ ሌላ ጭንቀት ሆኗል

ማሕደረ ዜና፣ የቀይ ባሕር አካባቢ መንግሥታት ዉስብስብ ግጭትና ዉጥረት
ነሐሴ ላይ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት አብዱረሕማን መሐመድ ኢሮ አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጉብኝቱ «በጠወለገዉ» የመግባቢያ ስምምነት ላይ ነብስ ከዘረባት እስካሁን ገሚስ የህወሓት መሪዎችን የክበቡ አካል ለማድረግ የሚዉተረተረዉ የሞቃዲሾ፣ ካይሮ፣ አሥመራ ገዢዎች አክሲስ ወይም ሥብስብ ምናልባት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ገሚስ መሪዎችን ሊያቅፍ፣ አጓጉል መዘዙ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን ሊደርስ ይችላል።

ማሕደረ ዜና፣ የጋዛ ተኩስ አቁም ተስፋ፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዕዉነታ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ዋሽግተን ዉስጥ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በሚያደርጉት ዉይይት ሁለቱ መሪዎች የዓመት ከዘጠኝ ወራቱን ወታደራዊ ዘመቻ ለ60 ቀናት ለማቆም ያላቸዉን ዕቅድ ያስታዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዩናይትድ ስቴትስና ቀጠር አቀረቡት የተባለዉን ሐሳብ እስራኤልም-ሐማስም ተቀብለዉታል ተብሏል።ሐሳቡ መፅደቅ-መዉደቁ የሚወሰነዉ ግን በትራምፕና በኔትንያሁ ትዕዛዝ ነዉ።

ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል፣ የአሜሪካና የኢራን የጦርነት ማግሥት የጦርነት ዝግጅት
በርግጥ ጀግናዉ ማነዉ? 12 ቀናት የቆየዉን፣ከ600 በላይ ኢራናዉያንን፣ 28 እስራኤላዉያንን የገደለዉን፣ የሁለቱን ሐገራት ምጣኔ ሐብት ያሽመደ።መደዉን ዉጊያ ቀድማ የከፈተችዉ እስራኤል ናት።ዩናይትድ ድብደባዉን ፈቅዳለች፣ ኋላ ራሷ ቀጠላበታለች።አሁን የሚሞጋገሱት የሁለቱ ጥብቅ ወዳጅ መንግሥታት መሪዎች ኢራንን ለመደብደባቸዉ የሰጡት ምክንያት የቴሕራንን የኑክሌር ተቋማት ለማዉደም ነዉ።ወሕኒ ቤት የኑክሌር ተቋም ይሆን?

ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ፣ መዘዙና ሕግ አልባዋ ዓለም
የቀድሞዉ የዶናልድ ትራምፕ የፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን ባንድ ወቅት «የዓለም ማሕበረሰብ የሚባል ነገር የለም።ያለችዉ አንድ ልዕለ ኃያል ሐገር ናት-ዩናይትድ ስቴትስ።» ብለዉ ነበር።አላበሉም።ዓለም የጋራ ማሕበር፣ ፍርድ ቤት፣ ሕግ፣ ደንብ፣ ሥምምነት የሚኖራት ለአሜሪካና ለእስራኤል እስከጠቀመ ብቻ ነዉ።ባይሆን ኖሮ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯ ከተወገዘ፣ በማዕቀብ ካስቀጣ፣እስራኤልና አሜሪካ ሊባኖስን፣የመንን፣ ሶሪያን፣ኢራንን መደብደባቸዉ፣ታጣቂዎችን ከሕሙማን ሳይለዩ መግደላቸው የማያስወገዝ፣ የማያስጠይቅ፣ የማያስቀጣበት ምክንያት የለም።

የእስራኤል ኢራን ጦርነት ዓለማቀፍ ስጋት ደቅኗል

ማሕደረ ዜና፤ ሊቢያ፣ ኃያላን ያወደሟት፣ታጣቂዎች የሚተራመሱ፣ ዘራፊዎች የሚሻሙባት ሐገር
የአሜሪካዉ ዜና አገልግሎት አሶስየትድ ፕሬስ በ2022 እንደዘገበዉ በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔ የዘመተዉ የኔቶ ጦር ከመርከብ የተኮሰዉ ሳይቆጠር በጦር ጄት ብቻ ሊቢያን 10ሺሕ ጊዜ ደብድቧል።በድብደባዉ የተገደለዉን ሰዉ ቁጥር እስከ 500,000 የሚያደርሱት አሉ።መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግን የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ቁጥርን ሲያንስ 70 ሲበዛ 403 ያደርሱታል።የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ምብቶች ምክር ቤት የኔቶ ጦር 60 ሰላማዊ ሰዎች መግደሉን አረጋግጧል።ሟች ቁስለኛዉ 60፣70፣400 ይሁን 500 መቶ ሺሕ ተጠያቂዎች ለፍርድ ቀርበዉ ይሆን? ሐገር ማፍረስስ ያስወነጅል ይሆን? አናዉቅም።ሊቢያ ግን በርግጥ ፈርሳለች።

የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትችትና ነቀፋ የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን?
ፐሬዝደንት ኢሳያስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወይም ባካባቢዉ የታወጀ ጦርነት አንድ አይደለም። «ብዙ ጦርነቶችን ለማስቀጠል ዘመናይ ቴክኖሎጂና ጦር መሳሪያ እየተሰበሰበ ነዉ» ብለዋል።የብልፅግና ፓርቲ ለቴክኖሎጂና ለጦር መሳሪያ የሚያወጣዉ ዶላርም ልክ የለዉም ብለዋል።ኢሳያስ «ርካሽ» ያሉት ፉከራና ቀረርቶ በእሳቸወ አገላለፅ ተመዝግቧል።«የኤርትራን ሕዝብና መንግሥትን ወደ ግጭት ለማስገባት የሚሸረበዉ ግልፅና ሥዉር ሴራን ያላወቀዉ የለም» ይላሉ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት።የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን?

ማሕደረ ዜና፣ የምርጫ 97 ሒደት፣ዉጤትና አሳዛኝ ፍፃሜዉ 20 ዓመት ደፈነ
ከ25 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅ ሰጥቶበታል።ሕዝባዊ፣ ታሪካዊ፣ አብነታዊም ነበር።የአሸናፊ-ተሸናፊዉ ዉዝግብ፣ የገዢዉ ፓርቲ ጨካኝ ርምጃና እስከዛሬ የተረፈዉ መዘዝ ሲጤን ግን ራቅ ሲል በ1953 በአፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ከሞከረዉ መፈንቅለ መንግስት፣ ቀረብ ሲል በ1969 በኮሌኔል መንሥቱ ላይ ከተሞከረዉ የግድያ ጥቃት ዉጤት ጋር የሚያመሳስሉት አሉ።

ማሕደረ ዜና፣ ሕንድና ፓኪስታን የዝንተ ዓለም ጠላቶች
የሒንዱ፣የሲክና የቡዳሐ አማኞች በብዛት የሚኖሩበት ግዛት ሕንድ ሲባል፣ ሙስሊሞች የሚበዙበት የዛሬዎቹ ፓኪስታንና ባንግላዴሽ ግዛቶች ደግሞ ፓኪስታን ሆኑ።ክፍፍሉ ሲደረግ ሙስሊሞች በብዛት የሚኖሩበት የጃሙ ካሽሚር ካሽሚር ግዛት ግን የሒንዱ እምነት የሚከተሉት የግዛቱ አገረ-ገዢ እንደጠየቁት ነፃ መንግስትም ሳይሆን፣ ከፓኪስታንና ሕንድም ሳይጠቃለል ለወደፊቱ ግጭት እንዲመች ተንጠልጥሎ ቀረ።

ማሕደረ ዜና፣ የፕሬዝደንት ትራምፕ ሠላም የማስፈን ቃልና ተቃራኒ ርምጃ
በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ደግሞ የእስራኤል ጦር ገና በቅጡ ያልጠናዉን የሶሪያ መንግስት ይዞታዎችን በተዋጊ ጄቶች ደብድቧል።እስራኤል ጋዛን፣ ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ዳርቻን ፣የመንን፣ ኢራንን፣ ሊባኖስን መናደፏ አልበቃ ብሏት በተለያዩ የሶሪያ ጎሳ ወይም የሐይማኖት ሐራጥቃ ተከታዮች መካከል በተነሳ ጠብ ጣልቃ ገብታ በ14 ዓመት ጦርነት የወደመችዉን ሶሪያን ደጋግማ መደብደቧ ለብዙ ታዛቢ ግራ አጋቢ ነዉ።ሶሪያዊ አዛዉንት እንደሚሉት ግን የእስራኤል ጥቃት በአረብ መሪዎች ዝምታ፤ በዶንልድ ትራምፕ ይሁንታ የታገዘ ነዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቃል፣ መርሕና እርምጃ ቁንፅል ትዉስታ
ሕይወቱን ለኃይማኖት ከሰጠ በኋላ ግን እንደ ድሆች ሁሉ ለስደተኞችም ሲሟገት አድጎ፣ጦርነትን ሲቃወም በስሎ አርጅተዋል። ፍራንሲስ። በ 12 ዓመታት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣናቸዉ ዘመን 68 ሐገራትንና በመቶ የሚቆጠሩ ግዛቶችን ጎብኝተዋል።ከሮም ዉጪ መጀመሪያ የጎበኙት ግን በአብዛኛዉ የአፍሪቃ ስደተኞችን የሜድትራንያንን ባሕር ለማቆረጥ ሲቀዝፉ በብዛት የሚልቁበትን ባሕር፣ ከዳኑ የሚያርፉበትን ደሴት ነበር።ላፔዱዛን ሐምሌ 8፣ 2013

ማሕደረ ዜና፣የሱዳን ዉድመትና የመከፋፈሏ ሥጋት
የለንደኑ ጉባኤ የተደረገዉ ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ያደረጁት «የሱዳን የሰላምና የአንድነት» ወይም የሱዳን ትዩዩ መንግሥት መመሥረቱ ናይሮቢ ላይ በታወጀ ማግሥት፣አል ቡርሐን የሚመሩት መንግስት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን በዘር ማጥፋት ወንጀል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍርድ ቤት ላይ በከሰሰ ሳልስት ነበር።ሚዚያ 16።ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመሯቸዉ ቡድናት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የገንዘብ ድጋፍ፣በኬንያዉ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ አስተናጋጅነት የትይዩ መንግስት መመሥረታቸዉን ግብፅና ሳዑዲ አረቢያ አዉግዘዉታል

ማሕደረ ዜና፣ የኢራን-አሜሪካ ድርድር ጠብ-ግጭቱን ያበርድ ይሆን?
የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ (MEK)ና የቡድኑ ምክር ቤት መሪዎች ኢራን በ1967 ከአሜሪካ ባገኘችዉ ድጋፍ የጀመረችዉን የኑክሌር መርሐ ግብርን ወደ ኑክሌር ቦምብ መስሪያነት ለመቀየር ናታንዝና አራክ ዉስጥ በድብቅ እያብላላች መሆኑን ለዓለም አረዱ።ወይም አበሰሩ።ነሐሴ 2003።ዋሽግተን።ሲሞን ሔርሽና ኮኒ ብሩክ የተባሉት መርማሪ ጋዜጠኞች እንደፀፋት የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ መሪዎች የቴሕራኖችን ሚስጥር እንዲያጋልጡ የገፋፏችዉ መረጃዉንም የሰጧቸዉ የእስራኤል ባለሥልጣናት ናቸዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ፍጥጫ-የመካከለኛዉ ምሥራቅ ምሥቅልቅል ሌላ ገፅታ
የቴሕራን የፖለቲካና የጦር ሹማምንት ደግሞ ለፕሬዝደንት ትራምፕ ዛቻ አፀፋ ዛቻ እየሰነዘሩ ነዉ።የአያቶላሕ ዓሊ ኻማኒይ የቅርብ አማካሪ አሊ ላርጃኒ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት ኢራን የኑክሌር ቦምብ መታጠቅ አትፈልግም።የአሜሪካኖች ዛቻ ከበረታ ግን ቀጠሉ የቀድሞዉ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ ተደራዳሪ «ሌላ ምርጫ የለንም---መታጠቅ እንጂ።»

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ
የብርቱካን ተመስገን ትረካ እዉነት-ሐሰትነት ለብዙዎች በጣሙን እሁለት ለተገመሱት ለማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ አስተያየት ሰጪ-ተከታታዮች ማከራከሩን እንደቀጠለ ነበር።ግን እንዲያዉ ለመጠየቅ ያሕል 120 ሚሊዮን የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐቁን የሚያወጣ አንድ መርማሪ ፖሊስ፣ አንድ መርማሪ የሕግ ባለሙያ፣ አንድ መርማሪ ጋዜጠኛ፣ አንድ የምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ እንዴት አጣ?

ማሕደረ ዜና፣ ሱዳኖች አንድም ሁለትም ሆነዉ ከግጭት-ጦርነት ያልተዩ ሐገራት
የማቻር ደጋፊ የሚባሉት የኑዌር ጉሳ ሚሊሻዎች ኢትዮጵያን በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢ ከሠፈረዉ ከፕሬዝደንት ሳልቫኪር መንግስት ጦር ጋር መዋጋት ከጀመሩ ሳምንት አልፈዋል።የጁባዎች ጠብ የናረዉ ጁባዎች ከጋራንግ ሞት በኋላ እንዳደረጉት ሁሉ ከአል በሽር መወገድ በኋላ ዋና እና ምክትል ሆነዉ የካርቱም ሪፐብሊካን ቤተ መንግስትን የተቆጣጠሩት የሱዳን ጄኔራሎች የገጠሙት ጠብ በጦር ሜዳዉም በፖለቲካዉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት መሆኑ ነዉ።የፈጥኖ ደራሹ ጦር ከደቡብ ሱዳን ቡድናት ካንደኛዉ ጋር ያለዉን ትብብር ከማጠናከርም አልፎ የትይይዩ መንግስት--- ዳርፉር ግዛት ሊመሰርት ይችላል የሚለዉ ግምትም እያየለ ነዉ

“መፈንቅለ-መንግሥት” ወይስ “ሕግ ማስከበር” የትግራይ ቅርቃር
የህወሓት አመራሮች ልዩነት ሲበረታ በደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ያለፈው የትግራይ ክልል ነዋሪ “ነገስ ምን ይፈጠራል?” በሚል “እየተሳቀቀ እንዲኖር” ተገዷል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ሥጋት “ሰዉ በጣም ተረባብሿል”፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ “መከፋፈል” ተፈጥሯል። ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው “የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበ” ነው።

ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየተንሸራተተች ይሆን?
ከኢትዮጵያ ድንበር 30 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ናስር ከተማ በደቡብ ሱዳን ጦር ሠፈር ላይ የተፈጸመ ጥቃት ጁባን ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ከቷታል። በናስር በሚገኝ የደቡብ ሱዳን የጦር ሠፈር ላይ ባለፈው ሣምንት ጥቃት የፈጸመው ዋይት አርሚ ተብሎ የሚጠራ የኑዌር ጎሳ ታጣቂ ቡድን ነው። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ምክትላቸው ሪየክ ማቻርን ሳያማክሩ የወሰዷቸው ርምጃዎችም ቅሬታ ፈጥረዋል። ሁለቱ የተፈራረሙት የሰላም ሥምምነት ፈርሶ ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት እንዳትገባ ሥጋት አለ።

ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ሶማሊያ ወዳጅነት ካንጀት ወይስ ካንገት?
የአዲስ አበባና የሞቃዲሾ መሪዎች የጠባቸዉን መሰረታዊ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ማስወገዳቸዉን በይፋ ሳይናገሩ በወር ዕድሜ ለመወዳደስ፣ መተቃቀፍ መነፋፈቅ መድረሳቸዉ በርግጥ ጉድ አጃኢብ ማሰኘቱ አልቀረም።ማስታወቂያ ሚንስትር ዳዉድ አዌስ እንደሚሉት ግን ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሥምምነት ተሰርዟል።አዲሱ የትብብር ምዕራፍ ለኢትዮጵያ ወደብ ሥለ ማስገኘት አለማስገኘቱ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም።የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የምክር ቤት አባልናየፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር አብዲ ቡባል እንደሚሉት ደግሞ መተማመንን ለመገንባት ከአዲስ አበባ-ሞቃዲሾ-አንካራ የሚባክኑት ባለሥልጣናት ወደብን በተመለከተ አሁንም አይተማመኑም

ማሕደረ ዜና፣ የሱዳን ትዩዩ መንግስት፣ ጦርነቱና የዉጪ ጣልቃ ገብነት
ጉባኤተኞቹ እንዳሉት ዓላማቸዉ የሱዳንን አንድነት፣ የሕዝቧን ሠላምና ደሕንነት በጋራ ማስከበር ነዉ።የጉባኤተኞቹን ዉሳኔ በንባብ ያሰሙት የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ መሪ ሳንዳል ሐጋር እንዳሉት ደግሞ ጦርነቶችን በሙሉ ለማቆም ቆርጠዋልምተባባሪዎቹ በአማላይ ቃላት የከሸኑትን ሥምምነትና ትብብር ገቢር ማድረግ አለማድረጋቸዉ በርግጥ አጠያያቂ ነዉ።ፈጥኖ ደራሹ ጦር ከቀድሞ ቀንደኛ ጠላቶቹ በተለይም ከSPLM-N ጋር መወዳጀቱ ግን የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኞች እንደሚሉት ከምዕራባዊ ሱዳን እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ጥግ፣ ከሊቢያ ጠረፍ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር በሚደርሱ አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ ይጠቅመዋል።

ማሕደረ ዜና፣ የሁለት ጉባኤዎች አጭር ወግ
የሐገራት መሪዎች፣ ሚንስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የማሕበራት ሊቃነ መናብርት፣ ባለሙያዎች፣ የሠላምን ጥቅም፣ የዴሞክራሲን ፋይዳ፣ ተባብሮ የመሥራትን አስፈላነትን፣ ግጭት፣ጦርነት፣ አለመግባባት ያደረሱና የሚያደርሱትን ጉዳት የሚገልፁ፣ዉብ፣አማላይ፣ ማራኪ ቃላትን በየአዳራሹ አዘነቡት።በነዚያዉ ቃላት ተጠዛጠዙባቸዉም።የአፍሪቃ መሪዎች ዉሳኔ፣ መግለጫ ከአዲስ አበባ ሲናኝ የሙኒክ ጉባኤተኞች የፕሬዝደንት ሼሴኬዲን ማብራሪያ ያዳምጡ ነበር።እዚያዉ ምሥራቃዊ ኮንጎ ግን በሩዋንዳ የሚደገፈዉ M23 አርብ የቡካቩ አዉሮፕላን ማረፊያን ቅዳሜ ከተማይቱን ተቆጣጠረ

ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ መርሕ፣ርምጃና ዉሳኔ ልማት ወይስ ጥፋት
የትራምፕን እርምጃ ከማንም ቀድመዉ የአሜሪካ ታማኝ፣ የቅርብ ወዳጆች ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይን ጨምሮ 79 መንግስታት አዉግዘዉታልፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈዉ 21 ቀናት ዉስጥ የወሰዷቸዉ እርምጃዎች፣ ያሰለፏቸዉ ዉሳኔዎችና ያፀደቋቸዉ ትዕዛዛት ነባሩን የዓለም ፖለቲካዊ ሥርዓት ግራ ቀኝ ያላጉ፣ የአሜሪካንን ተቀባይነት የሸረሸሩ፣ እርዳታ ተቀባዮችን፣ ሰጪዎችንም የሚጎዳ ነዉ።የተቀረዉ ዓለም በያለበት «አንድ እግር በርበሬ----»ን በተናጥል ከማላዘን ባለፍ እስካሁን ሰብሰብ ብሉ ጠንካራ አፀፋ ለመስጠት አልቃጣም ወይም አልቻለም።ትራምፕም ቀጥለዋል።መጨረሻቸዉ ነዉ-ናፋቂዉ።

ማሕደረ ዜና፣ የሱዳን ጦርነት ድል-ሽንፈት

ከጋዛ እስከ ዩክሬን ጦርነት ያልተለየዉ ዓለም ከአዉሽቪትስ ምን ተማረ?

የፕሬዝደንት ጆ ባይደን የካበተ ልምድ ጠቀመ ወይስ ጎዳ?

ሶሪያ፣ የባዐዝ ዉልደት-ፍፃሜም፣ የአረብ አንድነት ሥርዓተ ቀብር ምድር

የጀዋር መሐመድ ወደ ፖለቲካው መመለስ

ለኢትዮጵያ ቀውስ መፍትሔ ሳይበጅ፣ ግጭት ሳይቆም የሽግግር ፍትሕ ተጎጂዎችን ይፈውስ ይሆን?
በኢትዮጵያ የቀውስ አዙሪት ግድያ፣ አስገድዶ መደፈር እና መፈናቀልን ጨምሮ የተለያዩ ግፎች የተፈጸሙባቸው ዜጎች ፍትሕ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ጭምር ለሽግግር ፍትሕ እየተዘጋጀች ነው። የአማራ እና የኦሮሚያ ግጭት ሳይቆም፤ ሀገሪቱን ቀውስ ውስጥ ለከተቱ ፖለቲካዊ ልዩነቶችም መፍትሔ ሳይበጅ ተግባራዊ የሚደረግ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት በእርግጥ ተጎጂዎችን ለመፈወሱ በርካቶች ጥያቄ አላቸው።

ተዳፍኖ የቆየው የሶርያ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እያገረሸ ይሆን?
የሶርያ አማጽያን በፕሬዝደንት በሺር አል አሳድ መንግሥት ላይ የከፈቱት ጥቃት ተዳፍኖ የቆየውን የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየቆሰቆሰው ይገኛል። አማጽያኑ አሌፖን ተቆጣጥረው ሐማ ወደ ተባለች ከተማ ሲገሰግሱ ሶርያ እና ሩሲያ በአየር ከፍተኛ ድብደባ እየፈጸሙ ነው። የአሳድ አጋር ሒዝቦላሕ አሁን ተዋጊዎች ወደ ሶርያ የመላክ ዕቅድ እንደሌለው አስታውቋል። የሶርያን ጉዳይ የቀጠናው ሀገራት እና ልዕለ ኃያላን በእግር ጥፍራቸው ቆመው እየተከታተሉ ነው።
Empfohlen

Wikipedia Crime

Organisiertes Verbrechen - Recherchen im Verborgenen

Metamorphosis

Who cares?

Couch Safari - Abenteuer Afrika

NDR 1 Radio MV - Vorsicht Leif

Telephobia - Dieser eine Anruf

Fohlenfutter – der Borussia-Mönchengladbach-Podcast der RP

SWR3 Comedy

Der YeahFußball-Podcast

Frohe Botschaft - Der Islam Podcast

MJ Aktuell - by MALIBU * Ein Podcast zum King of Pop Michael Jackson